• ኢትዮ 360

በአባይ ግድብ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎችና ባለሙያዎች እየተወዛገቡ ናቸው።

Updated: Dec 22, 2019

ታሕሳስ 11/2012 ዓም


ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ውይይት በካርቱም ከተማ አካሄዱ።


The Ethiopian, Sudanese, and Egyptian ministers meet to discuss the Grand Renaissance Dam Photograph by Anadolu Agency

የሶስቱ ሀገራት ውሃ ሚኒስትሮች በካርቱም በግድቡ ውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ዙሪያ ትኩረት በማድረግ መወያየታቸው ተነግሯል።

የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ውሃ ሚኒስትሮች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በካርቱም ከተማ ያካሄዱት የሶስትዮሽ ውይይት ምን ውጤት እንዳስገኘ የተገለጸ ነገር የለም።


ይህ ውይይቱ በአለም ባንክ እና አሜሪካ ታዛቢነት ከሚካሄዱት አራት ስብሰባዎች ሶስተኛው መሆኑ ይታወቃል።

ይሕ በእንዲህ እንዳለ ሶስቱ ሀገራት ቀደም ሲል በነበረ ስብሰባቸው ማጠናቀቂያ ላይ ባወጡት መግለጫ የዓባይ ውሀ ተፈጥሯዊ ፍሰቱ በድርቅ ወይም በሌላ ምክንያት ቢዛባ ግብፅ ማግኘት ይገባኛል የምትለውን የውሀ መጠን እንዳይነካ ሽፋን የሚሰጥ መመሪያ ይዘጋጃል በሚል ያስገቡት ነጥብ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያን ተደራዳሪዎችና ባለሙያዎች እያወዛገበ መሆኑን ዋዜማ ረዲዮ ዘግቧል።


እንደ ዘገባው የኢትዮጵያ ወኪሎች በዚህ ላይ ተስማምተው መምጣታቸው እጅግ ስህተት መሆኑን ባለሙያዎች እየገለጹ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ በአባይ ውሀ ላይ ከታችኛው የተፋሰስ ሀገራት ጋር ስትወያይ ተፈጥሯዊ ፍሰት የሚባል ነገር ለውይይት እንኳ መቀበል

እንደሌለባት ነው አቋም ተይዞ የነበረው።

ምክንያቱም ተፈጥሯዊ ፍሰት ሲባል አንድ ወንዝ ላይ ምንም አይነት ሌላ መሰረተ ልማት የለም ማለት ሲሆን ፣ ኢትዮጵያ ደግሞ በአባይ ተፋሰስ ላይ ከህዳሴ ግድብ በፊት ጣና በለስ ፣ ፍንጫ፣ ጨርጨርና ቆጋ አይነት ግድቦችን ስለሰራች በተፋሰሱ ላይ ለሚደረጉ ስምምነቶች ተፈጥሯዊ ፍሰት የሚባል ነገር ሊመጣ አይችልም ባይ ናቸው።

በኢትዮጵያ በኩል ተፈጥሯዊ ፍሰት የሚባል ነገር የሶስትዮሽ የስምምነት መግለጫ ላይ እንዴት እንዲገባ ተፈቀደ የሚለው ግልጽ አይደለም። የኢትዮጵያና የግብጽ የድርቅ ትርጉም የተለያየ በሆነበት መልኩ ይህ የጋራ መግለጫ መውጣቱ ተገቢ አለመሆኑንም የዋዜማ ምንጮች ተናግረዋል።


ከዋሽንግተኑ ስብሰባ በሁዋላ የውሀ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትሩን ዶር ስለሺ በቀለን ጨምሮ ኢትዮጵያን የወከሉ የውሀ ሙያተኞች አንዴ ሱዳን ስለፈለገች ተስማምተናል ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ተፈጥሯዊ ፍሰት ለይ አልተነጋገርንም ነበር ግብጾች ናቸው መግለጫ ላይ ያስገቡት ብለው ሊያስተባብሉ ሞክረው ነበር።


ሆኖም የውሀ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ የሶስትዮሹ ስምምነት በዚህ መልኩ ሊቀጥል እንደማይገባ ድርድሩም እንዲቆም በኢትዮጵያ የቴክኒክ ሰዎች ተመክረው ነበር። ነገር ግን ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ለማወቅ ተችሏል።


እንደውም ባለፈው እሮብ በውሀ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስቴር በዚሁ ጉዳይ ባተኮረ ስብሰባ ላይ ሚኒስትሩ ዶክተር ስለሺ በቀለ ወይይቱ እየተመራበት ያለው መንገድ ለኢትዮጵያ አዋጭ አይደለም ይቁም በሚል ምክር የሰጧቸው የቴክኒክ ሰዎችን እንደዘለፏቸው ተዘግቧል። ስብሰባውንም አቋርጠው የወጡ ባለሙያዎች ነበሩ ተብሏል።364 views0 comments