• ኢትዮ 360

በኦሮሚያ ደምቢዶሎ የብሄር ጥቃት እየተፈጸመ ነው።

ታህሳስ 11/2012


በምዕራብ ኦሮሚያ ደምቢዶሎ ዞን የሌላ ክልል ተወላጆች ናችሁ በሚል እየተፈጸመ ያለው አሰቃቂ ግድያና ማፈናቀል እየተባባሰ መምጣቱ ተገለጸ።


በዞኑ ረቡዕ ገበያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢው ሰሞኑን ሁለት ሰዎች በስለት ታርደው እንዲገደሉ መደረጉ ውጥረቱን አባብሶታል ይላሉ የኢትዮ 360 ምንጮች።

ከባድ ድብደባ የደረሰባቸው እናትና አባቱን ለመጠየቅ ከደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን አቋርጦ የመጣው ልጃቸውም የወላጆቹ እጣ ፋንታ ደርሶት በደረሰበት ድብደባ ለከባድ ጉዳት መዳረጉንም ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል።


በደረሰን መረጃ መሰረት በአከባቢው ካለው ውጥረት ጋር ተያይዞ ከቀያቸው የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፥ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ እንኳ 200 የሚደርሱ ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ ሆኗል።


ምንጮቹ ለኢትዮ 360 እንደገለጹት የኦሮሚያ ክልል መታወቂያ የያዙና የክልሉ ነዋሪ መሆናቸው እየታወቀ ብሔራቸው ሊላ ነው በሚል ብቻ ይገደላሉ፥ይደበደባሉ፥ከቀያቸው እንዲፈናቀሉም ይደረጋሉ።


መንግስት የሚባል አካል ካለ ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ ከማለቃቸው በፊት መብታቸውን እንዲያስከብርላቸው ጥሪያቸውን አቅርበዋል።


3 views0 comments