• ኢትዮ 360

በአፋር ዴርኤብ ቀበሌ የኦሮሚያ ልዩ ሃይሎች አንድ አዛውንትን በጥይት አቆሰሉ።-ኢትዮ 360 ምንጮች

(ኢትዮ 360 - ታህሳስ 21/2012) በአፋር ዴርኤብ ቀበሌ የኦሮሚያ ልዩ ሃይሎች አንድ አዛውንትን በጥይት ማቁሰላቸው ተሰማ።

እንዲህ አይነቱ ጥቃት ሲፈጸም የዛሬው የመጀመሪያ አይደለም ይላሉ የአካባቢው ምንጮች ለኢትዮ 360።

የኦሮሚያ ክልል ወደ አፋር አዋሳኝ ወረዳዎች በየጊዜው ነዋሪዎቹን ለማስገባት የሚያደርገው ጥረት ለጥቃቱ ምክንያት ነው ይላሉ።

እንዲህ አይነቱ ወሰንን አልፎ የመግባት ልማድ ደግሞ ለግጦሽ ሳር ፍለጋ ሳይሆን ሁሉንም ሰብስቦ የመያዝና የመስፋፋት ፍላጎት ነው ብለዋል።

የዴርኤብ ቀበሌ ወደ አዋሽ አርባና አዋሽ ሰባት የመግቢያ ዋና ቁልፍ ቦታ በመሆኗ ሁልጊዜም የነእሱ የጥቃት ሰለባ ትሆናለች ሲሉ ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል።

እንዲህ አይነቱ ጥቃት ሲፈጸም ደግሞ የክልሉም ሆነ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ሳያውቁት የሚፈጸም ነገር የለም ይላሉ።

ነገር ግን ቢሰሙም እንዳልሰሙ ሆነው ንጹሃንን እያስፈጁ ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ መውቀሳቸውን መረጃዎቹ አመልክተዋል።

ነዋሪዎቹ ጨምረውም ድሮ በፍቅርና በሰላም የኖርን ዜጎች ዛሬ በመጣ ስልጣን ሁሉንም ሰብስቦ ለመውሰድ የሚደረገው ሙከራ አብሮ የሚያኖር አይደለምና ሊቆም ይገባዋል ማለታቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።4 views0 comments